ፌስቡክና ኢንስታግራም የአልኮልና ሲጋራ ማስታወቂያን የሚከለክል ህግ ይፋ አደረጉ

ፌስቡክና ኢንስታግራም በመተግበሪያቸው የሚከናወንን የአልኮልና ሲጋራ ማስታወቂያ የሚከለክል ህግ ይፋ አደረጉ።

ይፋ የተደረገው አዲሱ መመሪያ ዕድሜው 18 እና ከዛ በላይ የሆነ የመተግበሪያው ተጠቃሚ በገጹ ላይ ምንም አይነት የአልኮልና የሲጋራ ምርቶችን እንዳያስተዋውቅ የሚከለክል ነው ተብሏል።

በተጨማሪም መመሪያው በፌስቡክና ኢንስታግራም አማካይነት የአልኮልና ሲጋራ ሽያጭ እና የስጦታ ልውውጥን ጨምሮ የማስታወቂያ መልዕክቶችን የሚያግድ ነው፡፡

መመሪያው ከትናንት ጀምሮ በመተግበሪያው እና ምርቶቹን በሚያስተዋውቁ ተጠቃሚዎች ላይ ተግባራዊ መደረግ መጀመሩን ነው ሲኤንኤን በዘገባው አመልክቷል።

ለዚህም ኩባንያው የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን፣ የተጠቃሚዎችን ጥቆማ እንዲሁም የይዘት ቅኝት ሪፖርትን በግብዓትነት እንደሚጠቀም አስታውቋል።