ቻይና 46 ሺህ ቶን የሚመዝን የተሸከርካሪ ድልድይ ለትራፊክ ክፍት አደረገች

የድልድዩ ክብደት 46 ሺህ ቶን ሲሆን 263 ነጥብ 6 ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን÷በሰሜናዊ ቻይና የመጀመሪያውን የማጓጓዝ ስራውን በስኬት አጠናቋል፡፡

በድልድዩ የመጀመሪያ የሙከራ ስራ በ68 ደቂቃ ውስጥ ከቤጂንግ ጉንግዡ ባቡር ጣቢያ ባደረገው የማጓጓዝ ስራ በአካባቢው የነበረን በባቡርና ተሽከርካሪ የነበረን የትራፊክ መጨናነቅ እንዳቀለለ ተነግሯል፡፡

የድልድዩን የግንባታ ስራ የሰራው የደቡባዊ ቻይና የግንባታ ተቋራጭ የመሃንዲሶች ቡድን ነው፡፡ይህ ተንሸራታች ድልድይ  በስፋትና በክብደት አዲስ የአለም ክብረወሰን አስመዝግቧል፡፡

የድልድዩን ተጣጣፊ አካል የሚደግፈው ሉላዊ ማጠፊያ ድልድዪን ወደ ትኛውም አቅጣጫ ለማሽርከር እንዲያግዝ ሆኖ የተሰራ ነው፡፡

የድልድዩ ተሸከርካሪ አካል ማጠፊያም 6 ነጥብ 5 ሜትር ያህል ርዝመት ስላለው አዲስ ክብረወሰን አስመዝግቧል ተብሏል፡፡

ቻይና ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በገሪቱ የሚሰሩ ድልድዮችን ተንቀሳቃሽ በማድረግ  እየገነባች ትገኛለች ፡፡

ይህ የግንባታ ዘዴ በፍጥነት የሚጠናቀቅ ሲሆን  የትራፊክ ፍሰትን በማቅለል በኩልም ጉልህ ፋይዳ እንዳለው መነገሩን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡