የ30 አመት መረጃዎችን የሚያሳይ ዲጂታል የመሬት ምልከታ ቴክኖሎጂ በኢትዮጵያ ሊዘረጋ ነው

በዘርፉ የካበተ ልምድ ያላት አውስትራሊያ ይህንን የቴክኖሎጂ እውቀት ለኢትዮጵያ ለማካፈል ዝግጁ መሆኗን አስታውቃለች፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታው ጀማል በከር ቴክኖሎጂውን በኢትዮጵያ መዘርጋት በሚቻልበት ሁኔታ ዙሪያ ቴክሎጂውን በአፍሪካ ለመዘርጋት የሚንቀሳቀሰውን ቡድን ከሚመሩት ዶ/ር አዳም ሊውስ ጋር መክረዋል፡፡
ሚኒስትር ዴኤታው ቡድኑ በአፍሪካ ውስጥ የጀመረውን እንቅስቃሴ መሰረት አድርገው ለኢትዮጵያ ቅድሚያ ስጥተው እንዲሰሩ ጠይቀዋል፡፡
ቴክኖሎጂው የከርሰ ምድር ውሃና ማዕድን ያለበትን ቦታ መለየት የሚያስችል፣ የአፈር ሁኔታን ለመለየትና የደን ሃብትን ለመቆጣጠር የሚያስችል ነው፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር መረጃ እንደሚያሳየው ቴክኖሎጂው እስከ 30 አመት የሚደርሱ መረጃዎችንም ማሳየት የሚያስችል ነው፡፡
በዘርፉ ከፍተኛ ልምድ ካላት አወስትራሊያ ተሞክሮ ይወሰዳል ያሉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታው ጀማል በከር ከጂኦ ስፓሻል ኢንስቲቲዩት ጋር በቅንጅት በመስራት የቴክኖሎጂ ሽግግር ለመፍጠር ይሰራል ብለዋል፡፡