ፌስቡክ አዲስ የቪዲዮ የመልዕክት መለዋወጫ መሳሪያን ሊያስተዋውቅ ነው

ፌስቡክ  አዲስ የቪዲዮ የመልዕክት መለዋወጫ መሳሪያን ለደንበኞች ሊያስተዋውቅ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የኩባንያው ምክትል ፕሬዚዳንት በአሪዞና በነበራቸው ቃለመጠይቅ ወቅት  እንደተናገሩት፤ የመልዕክት መለዋወጫ መሳሪያው ከሁለት ወራት በኋላ ለገበያ ይቀርባል፡፡

ፌስቡክ ዋትስ አፕ፣ ሜሴንጀር እና ኢንስታግራምን ለመልዕክትና ምስል መለዋወጫነት እየተጠቀመ ሲሆን፤ በእነዚህ መተግበሪያ መሳሪያዎች የሚጠቀሙ ከ1 ቢሊየን በላይ ደንበኞች አሉት፡፡

አዲሱ መሳሪያ ጥሪዎችን ለማስተናገድ ጥቅም ላይ የሚውል ቢሆንም፤ መልዕክቶችን ለመቅዳት እንደማያስችል ኩባንያው ገልጿል፡፡

መሳሪያው በተለይም ምስጢራዊ መልዕክቶችን ለመለዋወጥ ተመራጭ ነው ብሏል ኩባንያው፡፡

ፌስቡክ በቅርቡ የተጠቃሚዎችን የግል መረጃ ያለ ፈቃዳቸው ለሦስተኛ አካል ማጋራት የሚከለክለውን ስምምነት በመጣሱ የ5 ቢሊየን ዶላር ቅጣት እንደተጣለበት ይታወሳል፡፡ ዘገባው የሲጂቲኤን ነው፡፡