464 ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲ አረቢያ መመለስ

ጳጉሜ 5/2013 (ዋልታ) በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ 464 ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲ አረቢያ ተመለሱ፡፡

በዚህም 110 ህጻናትን ጨምሮ 464 ዜጎች መመለሳቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

ተመላሾቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄነራል ተወካይ አቀባበል አድርገውላቸዋል።