5ቱ የጳጉሜ ቀናት መርሃ ግብሮች

ነሐሴ 26/2013 (ዋልታ) – የጳጉሜን 5 ቀናት የተቸገሩ ወገኖችን መርዳት፣ አብሮነት እና አንድነትን ማጉላት ላይ ባተኮሩ መርሃ ግብሮች ለማሳለፍ ዝግጅት ማጠናቀቁን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡
ዋልታ ከአስተዳደሩ ባገኘው መረጃ የ2014 አዲስ ዓመት አቀባበልን አስመልክቶ በ5ቱ የጳጉሜ ቀናት አገራዊ እና ከተማ ዐቀፋዊ ፋይዳ ያላቸው መርሃ ግብሮችን ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ለመከወን ተዘጋጅቷል፡፡
በቀናቱ ዝርዝር መርሃ ግብር ላይም አስተዳደሩ የፊታችን አርብ ነሐሴ 28 /2013 ማብራሪያ ይሰጣል ነው የተባለው፡፡