5 ሺሕ ሰዎች የተገኙበት የፍቅር ምሳ ግብዣ በደሴ ከተማ እየተካሄደ ነው

የካቲት 6/2014 (ዋልታ) የወሎ ሕዝብ በአንድነት የቀደመውን መልካም እሴት እንዲያስቀጥልና ደሴ ከተማ ያላትን ባሕልና ወግ ይዛ እንድትዘልቅ ዓላማ ያደረገ 5 ሺሕ ሰዎች የታደሙበት የፍቅር ምሳ ግብዣ በአይጠየፍ አዳራሽ እየተደረገ ነው፡፡

መርሃ ግብሩን የደሴ ከተማ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት አደራጅ ግብረ ኃይል እና በአዲስ አበባ የሚኖሩ የወሎ ባለሃብቶች በጋራ እንዳዘጋጁት አሚኮ ዘግቧል፡፡

በምሳ ግብዣው ላይ የሁሉም የሃይማኖት አባቶች፣ የደሴ ከተማ የሥራ ኃላፊዎችና ከሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል የተውጣጡ የከተማዋ ነዋሪዎች ተገኝተዋል፡፡