50 ሚሊየን የአፍሪካ ሴቶች ይናገሩ ፕሮጀክት በይፋ ተጀመረ

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ

መጋቢት 09/2013 (ዋልታ) – “50 ሚሊየን የአፍሪካ ሴቶች ይናገሩ” የደቡባዊ አፍሪካ አገሮች የጋራ ገበያ (ኮሜሳ) ፕሮጀክት በኢትዮጵያ በይፋ ተጀምሯል፡፡

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ፕሮጀክቱን በይፋ ባስጀመሩበት ወቅት ሴቶች በርካታ ችግሮችን  እንደሚጋፈጡ ገልፀው በኢኮኖሚው ዘርፍ ውጤታማና ተወዳዳሪ እንዳይሆኑም መሰናክሎች እንደገጠማቸው አስታውቀዋል፡፡

የብድር አቅርቦት እጦትና በተሰማሩበት ዘርፍ መረጃ አለማግኝት መሰናክል እንደሆኑባቸው የገለጹት ፕሬዝዳንቷ ፣ በሁሉም የኢኮኖሚ ዘርፎች የሴቶች ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ሀገራት ምቹ ሁኔታ መፍጠር ይገባቸዋል ብለዋል።

ፕሮጀክቱ በዋናነት ሴት የአፍሪካ ስራ ፈጣሪዎችን ለማበረታታት ያለመ ነው ተብሏል፡፡

በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ፣ የኢፌዴሪ የሴቶችና ወጣቶች ሚኒስትር ፊልሰን አብዱላሂ እንዲሁም የኮሜሳ አባል ሀገራት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችም ተገኝተዋል።

(በደረሰ አማረ)