5ኛው የምስራቅ አፍሪካ የፋይናንስ ጉባኤ እየተካሄደ ነው

ግንቦት 3/2014 (ዋልታ) 5ኛው የምስራቅ አፍሪካ የፋይናንስ ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

በጉባኤው የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴን ጨምሮ የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተወካዮች፣ የቴክኖሎጂ አቅራቢዎችና በምስራቅ አፍሪካና በውጭ የሚገኙ ቁልፍ የፋይናንስ ተቋማት ተገኝተዋል።

ጉባኤውን ጅማ ዩኒቨርስቲ፣ የኢትዮጵያ መድህን ሰጪዎች ድርጅት፣ የተመሰከረላቸው የሂሳብ ባለሙያዎች ማኅበር እና አይ ካፒታል ኢንስትቲዩት በጋራ ማዘጋጀታቸውም ተጠቁሟል፡፡

በጉባኤው በፋይናንስ ሥርዓቱ ላይ የተለያዩ ጥናቶች እንደሚቀርቡና የፋይናንስ ሥርዓት ፖሊሲ በስፋት እንደሚገመግምም ይጠበቃል።

በመስከረም ቸርነት