6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በካፋ ዞን በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች በሰላም መጠናቀቁ ተገለፀ

ሰኔ 15/2013 (ዋልታ) – 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በካፋ ዞን በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች በሰላም መጠናቀቁ ተገለፀ።

በአንዳነድ የምርጫ ጣቢያዎች የድምፅ አሰጣጡ እስከ ሌሊቱ ስድስት ሰዓት የዘለቀ ሲሆን፣ የምርጫ አስፈፃሚዎች እና ታዛቢዎች በከፍተኛ ፅናት የድምፅ ቆጠራን ሲያከናውኑ አድረዋል።

ቆጠራው በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች የተጠናቀቀ ሲሆን፣ ውጤቱም በምርጫ ጣቢያ ደረጃ እየተገለፀ ይገኛል።

በዞኑ ሰባት የፖለቲካ ፓርቲዎች ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለክልል ምክር ቤት ተወዳድረዋል።

(በአሳየናቸው ክፍሌ)