6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ብሩህ ተስፋን የሰነቀ ነው – የደሴ ከተማ ነዋሪዎች

ሰኔ 12/2013 (ዋልታ) – 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ብሩህ ተስፋን የሰነቀ ነው ሲሉ የደሴ ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ።

ከዚህ ቀደም የነበሩት ሀገራዊ ምርጫዎች የህዝብን ድምፅ ያላማከሉ እና በአንድ የፖለቲካ ፓርቲ የበላይነት የተመሰሉ የይስሙላ ምርጫዎች እንደነበሩ ያስታወሱት የከተማው ነዋሪዎች፣ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ይህን ስህተት ባለመድገም ህዝብን እና የህዝብን ጥያቄ ማዕከል ያደረገ ተስፋ የሰነቅንበት መሆኑን ለዋልታ ገልፀዋል።

በከተማዋ ያለውን የኑሮ ውድነት እንዲሁም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የስራ አጥነት ችግር ይፈታልናል ያልነውን የፖለቲካ ፓርቲ ድምፃችንን ተጠቅመን ለመምረጥ ተዘጋጅተናልም ብለዋል።

ምርጫ የህዝብ ፋላጎት የሚስተናገድበት፣ ሀገር ወደ ታቀደላት የእድገት ደረጃ ከፍ የምትልበት የሰላም መንገድ መሆኑን የተናገሩት የደሴ ከተማ ነዋሪዎች፣ ህዝቡ ይህን አውቆ ይበጀኛል ያለውን በድምፁ እንዲመርጥ ጥሪ አቅርበዋል።

(በቁምነገር አህመድ)