6ኛ ዕዝ ከፍተኛ ተጋድሎና ጀብድ ለፈፀሙ የማእረግ ማልበስ ሥነ-ሥርዓት እያካሄደ ነው

መጋቢት 11/2014 (ዋልታ) 6ኛ ዕዝ ከህግ ማስከበርና የኅልውና ዘመቻው ጀምሮ እስከ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት ዘመቻ ድረስ ከፍተኛ ተጋድሎ ላደረጉና ጀብድ ለፈፀሙ የሰራዊት ክፍሎች፣ አመራር እና አባላት የሜዳይና የማእረግ ማልበስ ሥነ-ሥርዓት እያካሄደ ነው፡፡
በሥነ-ሥርዓቱ የደቡብ ዕዝ ዋና አዛዥና የአድዋ ድል ከፍተኛ ሜዳይ ተሸላሚው ሌ/ጀኔራል ሰለሞን ኢተፋን ጨምሮ የክልል አመራሮች፣ ጀኔራል መኮንኖች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡