የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ደቡብ አፍሪካን ሊጎበኙ ነው

የናይጄሪያው ፕሬዚዳንት መሀመዱ ቡሃሪ ደቡብ አፍሪካን ሊጎበኙ ነው፡፡ ፕሬዚዳንቱ ደቡብ አፍሪካን ለመጎብኘት የተሰናዱት በደቡብ አፍሪካ በውጪ ሀገራት ዜጎች ላይ እየተፈፀመ ያለውን ጥቃት ተከትሎ ነው፡፡

በቀጣዩ ወር የሚደረገው የፕሬዚዳንቱ ይፋዊ ጉብኝት  የሀገራቱን ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ ስለመሆኑ የሲጂቲኤን ዘገባ ያመለክታል፡፡ ቀደም ሲል የናይጄሪያ ልዩ ልዑክ ከደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ጋር በሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ የመከረ ሲሆን፤ የፕሬዚዳንት ቡሃሪ ጉብኝትም የተጀመረውን የሁለትዮሽ ምክክር ይበልጥ መስመር ለማስያዝ እንደሚያስችል ይጠበቃል፡፡ ይሁንና የደቡብ አፍሪካው ኤምቲኤን ግሩፕ እና በሱፐርማርኬት የሚታወቀው ሾፕራይት በናይጄሪያ የሚገኙ ቅርንጫፎቻቸውን ዘግተዋል፡፡ ተቋማቱ በናይጄሪያ ቢሮዎቻቸው የሚሰሩ ሰራተኞች ላይ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ ነው ከዚህ እርምጃ ላይ የደረሱት ተብሏል፡፡

  • በናይጄሪያ በሚገኘው ኤምባሲዋ ላይ የአፀፋ ጥቃት በመሰንዘሩ ደቡብ
  • አፍሪካ በናይጄሪያ የሚገኘው ኤምባሲዋን መዝጋቷ እንዲሁም በደቡብ አፍሪካ በመኖርና በመስራት ላይ የሚገኙ ዜጎቼ

ስጋት ላይ ናቸው በሚል ናይጄሪያ ነፃ የአውሮፕላን ትኬት ማቅረቧ ይታወሳል፡፡ በደቡብ አፍሪካ በውጪ ሀገራት ዜጎች ላይ እየተፈፀመ ያለውን ጥቃት በርካታ ሀገራት ማውገዛቸውም አይዘነጋም፡፡