74 ኢትዮጵያዊያን ከሊባኖስ ተመለሱ

ሰኔ 17/2013 (ዋልታ) – 74 ኢትዮጵያዊያን ከሊባኖስ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡

በቤሩት የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽሕፈት ቤት ከሚመለከታቸው የሊባኖስ የመንግስት አካላት ጋር በመነጋገር ሰነድ አልባና የመኖሪያ ፍቃድ የሌላቸውን ዜጎች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ እያደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

ከቆንስላው ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ እንዳመላከተው ዛሬ ከተመለሱት መካከል 16 የሚሆኑ ዜጎች አሜል ኢንተርናሽናል የተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት የኮሮና ምርመራና የትኬት ወጪያቸውን ሸፍኗል፡፡