9 አገራት በኢትዮጵያ አዳዲስ አምባሳደሮችን ሾሙ

ታኅሣሥ 27/2014 (ዋልታ) ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ አዲስ የተሾሙ የ9 አገራትና የ1 ኅብረት አምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤ ተቀበሉ።
ፕሬዚዳንቷ ከአምባሳደሮቹ ጋር የተወያዩ ሲሆን ኢትዮጵያ ከአገራቱ ጋር ያላትን ወዳጅነት በተለያዩ ዘርፎች ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላት አጽንኦት ሰጥተዋል።
የጣሊያን፣ የማላዊ፣ የፍልስጤም፣ የጊኔ ቢሳው፣ የቡርኪና ፋሶ፣ የታንዛኒያ፣ የኩባ፣ የተባበሩት የአረብ ሊግ፣ የብሩንዲ እና የሴኔጋል አምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ በጽሕፈት ቤታቸው መቀበላቸውን የፕሬዝዳንት ጽሕፍት ቤት መረጃ ያሳያል፡፡