ሀገራቱ ወንጀልን በጋራ ለመከላከል የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ

መስከረም 11/2015 (ዋልታ) ኢትዮጵያ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ወንጀልን በጋራ ለመከላከል እና ተጠርጣሪዎችን አሳልፎ መስጠት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ስምምነቱን የኢትዮጵያ የፍትህ ሚኒስትር ዴኤታ አለምአንተ አግደው እና የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች የፍትህ ሚኒስትር አብደላ ሱልጣን አል ኑዋይሚ በአቡ ዳቢ ተፈራርመዋል፡፡

በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች የኢትዮጵያ አምባሳደር ሱሌማን ደደፎ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳሰፈሩት የእነዚህ ስምምነቶች መፈረም የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት የበለጠ እንደሚያጠናክረው ይታመናል።