ሀገርን ለማፈራረስ የተነሳውን ሽብርተኛው ህወሀት እስከወዲያኛው ለማጥፋት ዝግጁ ነን – ኮሚሽነር ዳመነ ዳሮታ

ነሀሴ 20/2013 (ዋልታ) – ሀገርን ለማፈራረስ የተነሳውን ሽብርተኛው ህወሀት እስከ ወዲያኛው ለማጥፋት ዝግጁ ነን ሲሉ የፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽ ኮሚሽነር ዳመነ ዳሮታ ገለጹ፡፡
ኮሚሽኑ ይህንን ያሉት የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን አዲሱን መለዮ የማዕረግና የደንብ ልብስ ባስተዋወቀበት መርሃግብር ነው።
ኮሚሽነሩ አክለውም በማረሚያ ቤቶች የነበሩ ክፍተቶች ለማረም በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ገልፀው የደንብ ልብሱ እና የማዕረግ እድገት በማረሚያ ቤቶች ለመጣው ለውጥ አመላካች መሆኑን አንስተዋል።
ኮሚሽነር ዳመነ ሀገር የገጠማትን ጡት ነካሽና አሸባሪ ለመገርሰስ የሁሉም ርብርብ የሚጠየቅበት ጊዜ እንደመሆኑ የማረሚያ ቤት ኮሚሽኑ ሀገርን ለመታደግ ዝግጁ መሆኑንም ተናግረዋል።
የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ ዋና አቃቢ ህግ ዶ/ር ጌዲዎን ጢሞቲወስ በበኩላቸው በማረሚያ ቤቶች የተደረገው ለውጥ የአልባሳት ብቻ አለመሆኑን ገልፀ፤ ማረሚያ ቤቶች ዜግች የሚታጎሩባቸው ማዕከላት ሳይሆን በስነልቦና የጠነከረ አምራች ዜጎች ሆነው የሚወጡበት ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል።
(በዙፋን አምባቸው)