“ሁል ጊዜ የማስባትን ሀገሬን በማየቴ ደስ ብሎኛል” ጋዜጠኛ ሄርሜላ አረጋዊ  

ጋዜጠኛ ሄርሜላ አረጋዊ

ታኅሣሥ 27/2014 (ዋልታ) የመንግሥትን የ1 ሚሊዮን ዲያስፖራዎች ጥሪ ተቀብላ ኢትዮጵያ የገባችው ጋዜጠኛ ሄርሜላ አረጋዊ “ሁል ጊዜ የማስባትን ሀገሬን በማየቴ ደስ ብሎኛል” አለች፡፡

ስለተሰጠኝ ፍቅርና ስላደረጋችሁልኝ አቀባበል አመሠግናለሁ ያለችው ጋዜጠኛ ሄርሜላ “ለዚች ሀገር ብሩህ ተስፋ ነው የሚታየኝ፤ ሁሉም ሰው ያደረገው የ#nomore (በቃ) እንቅስቃሴ የሚበረታታ ነው” ብላለች፡፡

ጋዜጠኛዋ ከደቂቃዎች በፊት አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም ዐቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ስትደርስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ አቀባበል አድርገውላታል።

በሰለሞን በየነ