ለ18ኛው የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ተሳታፊ ልዑክ ሽኝት ተደረገ

መጋቢት 5/2014 (ዋልታ) ኢትዮጽያ ለ17ኛ ጊዜ ለምትሳተፍበት የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን ለሚወክሉ አትሌተቶች እና ልዑካን የሽኝት እና የእራት ግብዣ ተደረገ።

በውድድሩ ላይ እንደ በሪሁ አረጋዊ፣ ለሜቻ ግርማ እና አክሱማዊት አምባዬ ያሉ ጥሩ አቋም ላይ የሚገኙ አትሌቶች እንደሚሳተፉ ታውቋል።

በመርኃ ግብሩ ላይ የተገኙት አምባሳደር መስፍን ቸርነት በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ የምትገኘውን ኢትዮጵያን የሚያስደስት ጥሩ ውጤት ይዘው እንዲመጡ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በአደራ ተረክበው የተሸኙት አትሌቶቹ ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ የተቻላቸውን ሁሉ ለማድረግ እንደሚጥሩ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በ17 የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ተሳትፋ 44 ሜዳሊያ በማግኘት ከአሜሪካ እና ሩሲያ ቀጥሎ ሶስተኛ ቦታ ላይ ትገኛለች።

18ኛው የዓለም የቤት ውስጥ የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ሠርቢያ ቤልግሬድ ላይ እንደሚካሄድም ተገልጿል።

በትዝታ ወንድሙ