ግንቦት 26/2014 (ዋልታ) የፌደራል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ለ55 ከፍተኛ መኮንኖች የእስትራቴጂክ የማዕረግ እድገት ሰጠ።
12ቱ ከረዳት ኮሚሽነርነት ወደ ምክትል ኮሚሽነርነት የተሸጋገሩ ሲሆን 43 የሚሆኑት ደግሞ ከኮማንደርነት ወደ ረዳት ኮሚሽነርነት ማዕረግ የተሰጣቸው መሆናቸው ተነግሯል፡፡
የእስትራቴጂክ ማዕረግ እድገቱ የተሰጣቸው ከፍተኛ መኮንኖች በሥራቸው በተግባር ተፈትነው ያለፉ፣ በትምህርት ዝግጅታቸው የመጀመሪያ ዲግሪ እና ከዛ በላይ ያላቸው፣ በመምሪያ ኃላፊነት 4 ዓመት ያገለገሉ እና በሥራቸው በሰራዊቱ ዘንድ የተመሰከረላቸው እንደሆኑም ተጠቅሷል።
የማዕረግ እድገቱ የተሰጠው ከፌደራል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ፣ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ እና ከድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ነው።
በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጨምሮ ሌሎች የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
በምንይሉ ደስይበለው