ለሀገራችን የሚመጥን አየር ኃይል ለመገንባት እየተሠራ ነው – ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ

ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ

የካቲት 20/2014 (ዋልታ) ለሀገራችን የሚመጥን አየር ኃይል ለመገንባት እየተሠራ ነው ሲሉ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ አየር ኃይል ዋና አዝዥ ሌተናል ጄኔራል ይለማ መርዳሳ ተናገሩ።

በለውጡ ዓመታት ድንቅ ውጤቶች ተመዝግበዋል ያሉት ሌ/ጄ ይልማ ተቋሙን የማጠናከር ሥራዎች እየተሠሩ ስለመሆናቸውም አንስተዋል፡፡

በህግ ማስከበር ዘመቻው የጠላት ምሽግ ሰብሮ በመግባትና በመደምሰስ የአየር ኃይል የፈጸመው ገድል ውጤታማ እንደነበረም አስታውሰዋል፡፡

ለዚህም በጀግንነት ለተሠዉ፣ ለቆሰሉ እንዲሁም በሥራ አፈጻፀም የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ማዕረግ የማልበስ መርሃ ግብር ማካሄድ አስፈላጊ ሲሉ ገልፀዋል፡፡

በሕግ ማስከበርና በኅብረ ብሔራዊ አንድነት ዘመቻው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ዕውቅና የመሥጠት መርሃ ግብር በአየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ በዛሬው ዕለት ተከናውኗል፡፡

ለአገር ሉዓላዊነት የሰው ኃይል በማፍራት እንዲሁም አየር ኃይሉ የሚሠጠውን ተልዕኮ ለመወጣት ተቋሙ ዝግጁ ስለመሆኑም አመልክተዋል፡፡

የዘላቂ ተቋም ግንባታ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል ሲሉም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ አየር ኃይል ዋና አዝዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ተናግረዋል፡፡

በሰለሞን በየነ