ለህዝባችን ዘላቂ ሰላም ያስፈልገዋል-ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ

ሐምሌ 14/2016 (አዲስ ዋልታ) ለህዝባችን ዘላቂ ሰላም ያስፈልገዋል ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ፡፡

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ በ7ኛው የጨፌ ኦሮሚያ ጉባዔ ለአሸባሪው የሸኔ ኃይል የሰላም ጥሪ አቅርበዋል።

አሸባሪው የሸኔ ቡድን የኦሮሞ ህዝብን ሰላም እያወከ መሆኑን አስታውሰው ከዚህ ተግባሩ በመቆጠብና ሰላማዊ መንገድ በመምረጥ ወደ ማህበረሰቡ በመመለስ በክልሉ ልማት ላይ እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል።

ለህዝባችን ዘላቂ ሰላም ያስፈልገዋል ያሉት ፕሬዝዳንቱ ፀጥታን ለማወክ ከሚጥሩ አካላት ጋር መንግስት ሰላም ለመፍጠርና የህዝቡን ደህንነት ለመጠበቅ አሁንም ከየትኛውም አካል ጋር ለመነጋገር ዝግጁ ነው ብለዋል።

ለመንግስትና ህዝብ የሰላም ጥሪ ዝግጁ ሆነውና ሰላማዊ መንገድን መርጠው ወደ ማህበረሰቡ ለተመለሱ አካላት የክልሉ መንግስትና ህዝብ ትልቅ ክብር ያለው መሆኑንም ጠቅሰዋል።

ይሁንና የሚደርግላቸውን ጥሪ ችላ በማለት የጥፋት መንገድን በመረጡ አካላት ላይ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በመጨረሻም የጨፌ ኦሮሚያ ጉባኤ በፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ የቀረበውን የ2016 የስራ ክንውን እና የ2017 የስራ እቅድ ሪፖርት ላይ በመወያየት በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።

በታምራት ደለሊ /ከአዳማ