ለመከላከያ ሰራዊት የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የይርጋጨፌ ነዋሪዎች ገለፁ

ነሀሴ 21/2021 (ዋልታ) – ህወሓትና ሸኔ ከኢትዮጵያ እስኪጠፋ ለመከላከያ ሰራዊት የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የይርጋጨፌ ነዋሪዎች ገለፁ፡፡

ህወሓት ባለፉት 27 ዓመታት ኢትዮጵያን በብሄርና በጎሳ በመከፋፈል የግል ፍላጎቱን ለማሳካት የተለያዩ ድርጊቶችን መፈፀሙ ሳያንስ አሁን ላይ ስርዓቱን እንዲጠቀም እድል አንሰጥም ማለታቸውን ከጌዴኦ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ መረጃ አመላክቷል፡፡