ለመከላከያ ሰራዊት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ድጋፍ

ጳጉሜ 03/2013 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለመከላከያ ሰራዊት የ60 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ።

የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች ያደረጉትን የአንድ ወር ደመወዝ ድጋፍ ላይ ዩኒቨርሲቲው 10 ሚሊየን ብር በመጨመር ድጋፍ መደረጉ ነው የተገለጸው።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጣሰው ወልደሃና (ፕ/ር) ድጋፉን ለኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር ቀንአ ያደታ (ዶ/ር) አስረክበዋል።

ሚኒስትሩ ለተደረገው ድጋፍ አመስግነው ለሰራዊቱ የሞራል ስንቅ እንደሚሆንም ጠቅሰዋል።

የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እስካሁን የ240 ሚሊየን ብር የዓይነት እና የገንዘብ ድጋፍ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ማድረጋቸውንም ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

የዓይነት እና የገንዘብ ድጋፍ ማድረጋቸውንም ሚኒስትሩ አስታውሰዋል።

 

በትዕግስት ዘላለም