ለባይደን አስተዳደር ድምጽ የሰጡ ኢትዮጵያዊያን እንቅስቀዋሴ አስፈላጊ ነው ተባለ

ለአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን መመረጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የነበራቸው ከ800 ሺሕ በላይ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ድምጻቸውን ማሰማት መጀመር እንዳለባቸው የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበራት ጥምር ሰብሳቢ ሶስና ወጋየሁ አስታወቁ።
የጥምረቱ ሰብሳቢዋ እንደገለጹት በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ብቻ ለባይደን መንግስት መመረጥ ከፍተኛ የሆነ ሚና ነበራቸው።
ከ800 ሺሕ በላይ ኢትዮጵያውያን የባይደንን አስተዳደር መርጠዋል፤ የኢትዮጵያን ዳያስፖራ ድምጽ ባያገኙ ወደ ስልጣን ላይመጡ ይችሉ ነበር ማለታቸውን የኢፕድ ዘገባ አመልክቷል።
በኢትዮጵያ ላይ የሚደረገውን ጫና ለማስቆም እነዚህ ድምጾች ከምን ጊዜውም በላይ ተጠናክረው መንቀሳቀስ መጀመር አለባቸው ያሉት ሰብሳቢዋ፣ ድምጽ የሰጡ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የመንግስት አቋምን የማስቀየር አቅም አላቸው ብለዋል።
ለባይደን መንግስት ድምጽ የሰጡ ኢትዮጵያውያን ዳያስፖራዎች አንድ መንግስት ላይ ከፍተኛ የሆነ ጫና የማሳደር ጉልበት አላቸውም ተብሏል።