ለቦረና ድርቅ ተጎጂዎች የመኖ ድጋፍ ተደረገ

ጥቀምት 13/2014 (ዋልታ) የግብርና ሚኒስቴር በቦረና በተከሰተው ድርቅ እንስሳትን ከከፋ ጉዳት ለመታደግ ከ18 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለውን መኖ ወደ ቦረና ዞን እያጓጓዘ መሆኑን አስታወቀ።

በሚኒስቴሩ የእንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ፕሮጀክት ብሔራዊ አስተባባሪ ቶማስ ቸርነት (ዶ/ር) እንደገለጹት በቦረና ዞን የተከሰተው ድርቅ በእንስሳት ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው።

በመሆኑም በምስራቅ ሸዋ ዞን ሞጆ፣ ወለንጭት፣ ሰበታና ሆለታ በአራት ማዕከላት የተዘጋጀ 77 ሺሕ እስር መኖ ዛሬ መላኩን ኢዜአ ዘግቧል።