ለትራፊክ ተጎጂዎች የደም ልገሳ፣ ማዕድ ማጋራት እና የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ

ጳጉሜ 4/2014 (ዋልታ) የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ለትራፊክ ተጎጂዎች የደም ልገሳ፣ማዕድ ማጋራት እና የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ።

የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ጳጉሜ 4 እየተከበረ የሚገኘውን <<የአገልጋይነት ቀን>> ምክንያት በማድረግ በአቤት ሆስፒታል ለትራፊክ ተጎጂዎች የደም ልገሳ፣ ማዕድ ማጋራት እና የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።

አራት ዊልቸር፣ ሁለት የህሙማን አልጋ ድጋፍ የተደረጉ የህክምና ቁሳቁስ ሲሆኑ ከተሽከርካሪ አደጋ ጋር በተገናኘ በሆስፒታሉ በህክምና ላይ ለሚገኙ 50 ህሙማንም ማእድ አጋርተዋል።

የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ሰራተኞችም ለትራፊክ አደጋ ተጎጂዎች እንዲሁም ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አድርገዋል።

በትዕግስት ዘላለም

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW