ለኅልውና ዘመቻው ከ6 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ተደረገ

ነሐሴ 26/2013 (ዋልታ) – የምዕራብ ሸዋ ዞን የመንግሥት ሰራተኞችና አመራሮች ለኅልውና ዘመቻው ከወር ደመወዛቸው ከ6 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ።

የዞኑ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ተስፋዬ ሚሬሳ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ለኅልውና ዘመቻው የሚደርገው ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ዙሪያ የመከሩት ሰራተኞቹና አመራሮቹ የአሸባሪዎቹን ሕወሓትና ሸኔን የጥፋት ጥምረት እንደማይቀበሉ የጋራ አቋም በመያዝ ውይይታቸውን አጠናቀዋል፡፡

በተመሳሳይ ዜና ሽብርተኛው ሕወሓት በሕዝብ ላይ እያደረሰ ያለው ስደትና መፈናቀል እንዳሳዘናቸው በቦረና ዞን የተልተሌ ወረዳ የመንግሥት ሰራተኞችና አመራሮች ገልጸዋል።

ሰራተኞቹና አመራሮቹ ባደረጉት ውይይት ለመከላከያ ሰራዊት ከወር ደመወዛቸው ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋልም ተብሏል።