ለአብርሆት መጻሕፍትን ለማሰባሰብ የሙዚቃና የኪነ-ጥበብ መርኃ ግብር ሊዘጋጅ ነው

የኪነ-ጥበብ መርኃ ግብር

ግንቦት 13/2014 (ዋልታ) ግራዝማች ኢንተርተይመንት ለአብርሆት ቤተ መጻሕፍት 20 ሺሕ መጻሕፍትን ለማሰባሰብ የሙዚቃና የኪነ-ጥበብ መርኃ ግብር ሊያዘጋጅ መሆኑ ተገለፀ፡፡

የሙዚቃና የኪነ-ጥበብ ዝግጅት መግቢያ ዋጋው ሁለት መጻሕፍት ሲሆን በዚህም 20 ሺሕ መጻሕፍትን ለማሰባሰብ ታቅዷል ነው የተባለው፡፡

መርኃ ግብሩ ሰኔ 5 እንደሚካሄድና የደም ልገሳ መርኃ ግብርንም ያካተተ መሆኑ ተገልጿል፡፡

“ሚሊዮን መጻሕፍት ለሚሊኒየሙ ትውልድ” እና “መጻሕፍትን በቤተ መጻሕፍት ውስጥ አኑሩ” በሚል መሪ ቃል ከሚያዝያ 28 እስከ ግንቦት 29 2014 ዓ.ም የተጀመረው የመጻሕፍት ማሰባሰብ መርኃ ግብር እንደ ቀጠለ ነው፡፡

ይህንንም ተከትሎ ግራዝማች ኢንተርተይመንት ለአብርሆት ቤተ መጻሕፍት መጻሕፍትን ለማሰባሰብ የሙዚቃና የኪነ-ጥበብ መርኃ ግብር ማዘጋጀቱን ይፋ አድርጓል፡፡

ኅብረተሰቡም ማጻሕፍትን ከመለገስ ጎን ለጎን ደም በመለገስ በደም እጦት ለሚሰቃዩና ሕይወታቸውን የሚያጡ ዜጎችን እንዲታደግ ጥሪ ቀርቧል፡፡

በመርኃ ግብሩ ላይ መገኘት የማይችሉ ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል ከሰኞ ጀምሮ መጻሕፍትን እንዲለግስና ትውልድን በማነፁ ሂደት አሻራውን እንዲያኖር ተጠይቋል።

በአሳንቲ ሀሰን

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW