ለአብርኆት ቤተ መጻሕፍት የመጽሐፍ ማሰባሰቢያ መርኃ ግብር እየተካሄደ ነው

ሚያዝያ 28/2014 (ዋልታ) – ለአብርኆት ቤተ-መጻሕፍት የሚሆን “አንድ ሚሊዮን መጽሐፍ ለሚሊዮን ትውልድ” በሚል ከሚያዝያ 28 እስከ ግንቦት 29 ለአንድ ወር የሚቆይ የመጻሕፍት ማሰባሰቢያ መርኃ ግብር ተጀመረ።
በመክፈቻ መርኃ ግብሩ ላይ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና ተማሪዎች ተገኝተዋል፡፡

በሳራ ስዩም

ለፈጣን መረጃዎች፦
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!