ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የውሃ ሃብት አስተዳደር በሚል ምክክር ተካሄደ

የካቲት 25/2014 (ዋልታ) ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የውሃ ሃብት አስተዳደር በሚል ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር ተካሄደ።

ዓለም ዐቀፍ የውሃ አስተዳደር ተቋም (ኢውሚ) ባዘጋጀው መድረክ ላይ ውሃ አጠቃቀማችንን እንዴት ዘመናዊ ማድረግ እና እየጨመረ የመጣውን የአየር ንብረት ለውጥ መከላከል እንችላለን በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ ነው ምክክሩ የተካሄደው።
በምክክር መድረኩ የተገኙት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ አብርሀ አዱኛ (ዶ/ር) ውሃን ተጠቅመን እንዴት የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም እንችላለን በሚለው ላይ ሚኒስቴሩ የተለያዩ የመጠጥ ውሃ ፖሊሲና ስትራቴጂ ቀርፆ እየሠራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በምክክሩ ላይ ከባቢ የአየር ንብረት ለውጥ በውሃ ላይ ጉዳት እንደሚያስከትል የተገለፀ ሲሆን ውሃን እንዴት ዘመናዊ በሆነ መንገድ ተጠቅመን ማኅበረሰቡን መጥቀም ይቻላል የሚለው ደግሞ የምክክሩ ዋነኛ ዓላማ ነው ተብሏል።
በሱራፌል መንግሥቴ