ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን በአሜሪካ የምስጋናና የእራት ግብዣ ተደረገለት

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን

ሐምሌ 20/2014 (ዋልታ) የ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናን በድል ላጠናቀቀው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን በአሜሪካ የምስጋናና የእራት ግብዣ ተደረገለት፡፡

ለአትሌቲክስ ቡደኑ ትላንት ምሽት ግብዣውን ያደረጉት በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር)፣ በተባበሩት መንግሥታት የኢትዮጵያ ቋሚ መልእክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ፣ በኒው ዮርክ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቢሮ እና የኢትዮጵያ ኮሙዩኒቲ አባላት በጋር በመሆን ነው።

በአቀባበሉና በግብዣው ሥነ ሥርዓት ላይም የአትሌቲክስ ቡድኑ በኦሪገኑ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ በመሳተፍ በታሪኩ ከፍተኛ የሆነውን ውጤት በማስመዝገቡ እንኳን ደስ አላችሁ ተብሏል፡፡

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን በሻምፒዮናው 4 ወርቅ፣ 4 ብር እና 2 ነሐስ በድምሩ 10 ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ በማምጣት ከአሜሪካ በመቀጠል ከዓለም 2ኛ በመውጣት ማጠናቀቁ ይታወሳል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
ቲዊተር https://twitter.com/walta_info
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!