ለኢትዮጵያ ክብር ስል መሞትን እመርጣለሁ ሲል ኬኒያዊ ላቫኒ ሚላ ገለጸ

ኅዳር 21/2014 (ዋልታ) ኬኒያዊው ላቫኒ ሚላ “ለኬኒያ ያለኝ አገራዊ ፍቅር ከኢትዮጵያ የበለጠ አይደለም፤ ለኢትዮጵያ ክብር ስል መሞትን እመርጣለሁ” ሲል ገለጸ፡፡

የተወለድኩትም ሆነ የምኖረው ኬኒያ ቢሆንም ኢትዮጵያን ሲጎዷት ሁላችንንም ነው የሚጎዱት ብሏል፡፡

በኢትዮጵያ ዕድገት ሳይኖር በኬኒያ ዕድገት ሊታሠብ አይችልም፤ ለኢትዮጵያ ክብር ስል መሞትን እመርጣለሁ ሲል በትዊተር ገጹ ላይ አስፍሯል።

ኃይሌ ገ/ሥላሴ ወደ ጦር ግንባር እዘምታለሁ ማለቱን ተከትሎ በአንዳንድ አለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን የሚሰራጨው ዘገባ አስገራሚና የሚደንቅ ቢመስልም ለአንድ አፍሪካዊ ጀግና የተለመደ ድርጊት ነው ብሏል፡፡

ሁላችንም የበለጸገችና ሠላማዊ ኢትዮጵያን እንመኛለን፤ ኢትዮጵያ የአሜሪካን የውክልና ጦርነት ታሽነፋለች ሲልም ገልጿል፡፡