ሉሲዎቹ ከ2022 የአፍሪካ ሴቶች ዋንጫ ውጪ  ሆኑ

ጥቅምት 16/2014 (ዋልታ) በሴቶች አፍሪካ ዋንጫ የመጀመርያ ዙር ማጣርያ የመልስ ጨዋታ ኢትዮጵያ ዩጋንዳን 2 ለ 0 ማሸነፍ ብትችልም በድምር ውጤት ሉሲዎቹም ከ2022 የአፍሪካ ሴቶች ዋንጫ ውጪ ሆነዋል።
ኢትዮጵያና ዩጋንዳን በድምር ውጤት 2 እኩል መሆናቸውን ተከትሎ በተሰጠ የመለያ ምት ዩጋንዳ 2 ለ 1 በማሸነፏ ሉሲዎቹ ከ2022 የአፍሪካ ሴቶች ዋንጫ ውጪ መሆናቸው ተገልጿል።