ሊጉ ግጭት በተቀሰቀሰበት አካባቢ በሴቶችና ህፃናት የሚደርሰው ግፍ እንዲቆም አሳሰበ

ሰኔ 16/2014 (ዋልታ) የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ግጭት በተቀሰቀሰበት አካባቢ በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚደርሰው ግፍ እንዲቆም መንግሥት አስፈላጊውን እርምጃ ሊወስድ እንደሚገባ አስታውቋል።

በወለጋና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከጥቂት ቀናት በፊት የተፈፀመውን ግፍ ሊጉ አውግዟል።

ሊጉ በሀዋሳ ለአራት ቀን የሚቆይ ከመላው የሀገሪቱ ክፍል የተወጣጡ ከ1 ሺሕ 200 በላይ ሴቶች የሚሳተፉበት ጉባኤ እንደሚያካሂድ ገልጿል።

በጉባኤው በሰላምና ደኅንነት ላይ፣ በመልካም አስተዳደር፣ በኑሮ ውድነት እንዲሁም የሴቶች ተሳትፎና መሰል ጉዳዮች ላይ እንደሚመክር አስታውቋል።

ሊጉ በአራት ቀን ቆይታው የሚመሩት እጩዎችን አቅርቦ ይመርጣልም ተብሏል።

በዙፋን አምባቸው