ሌተናል ጀነራል በጫ ደበሌ የውስጥ አሸባሪና የውጭ ጋላቢዎቻቸውን እየተዋጋን ነው አሉ

ሌተናል ጀነራል በጫ ደበሌ

ኅዳር 24/2014 (ዋልታ) የምትዋጉት አሸባሪውን ብቻ ሳይሆን ጋላቢዎቻቸውን ጭምር ነው ሲሉ የመከላከያ ሚኒስቴር የሰራዊት ግንባታ ሥራዎች ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጄነራል በጫ ደበሌ ገለጹ፡፡

ሌተናል ጄነራል በጫ ደበሌ በጭፍራ ግምባር ተገኝተው ለሰራዊት አባላት ንግግር አድርገዋል።

ባደረጉት ንግግርም የሰራዊት አባላቱ ጀግኖች እንደሆኑ በመግለፅ “የምትዋጉት አሸባሪውን ብቻ ሳይሆን ጋላቢዎቻቸውን ጭምር ነው” ብለዋል ።

የውስጥ ኃይሎች ለውጪ ወኪል ሆነው ኢትዮጵያን በሚወጉበት ወቅት በአንድነት ተነስተን አሸባሪዎችን ድባቅ እንመታለን ነው ያሉት።

ይህ ትውልድ በዚህ ታሪካዊ ወቅት አሸባሪውን የመቅበር እድል በማግኘቱ ሊደሰት ይገባል ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የተገኘው መረጃ ይጠቁማል።

የአፋር ክልል ርዕሰ መስተደድር አወል አርባ እና አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ በስፍራው በመገኘት ሰራዊቱን አበረታተዋል።