ሎውረንስ ፊሪማን አዲስ አበባ በውጭ አገራት ከተከፈተባት የስነልቡና ጦርነት ውጭ የተረጋጋች ነች አሉ

ሎውረንስ ፊሪማን

.”እዚህ አፍጋኒስታን የለም፤ የመንግሥት ለውጥም አያስፈልግም”

ኅዳር 20/2014 (ዋልታ) የአፍሪካ ፖሊሲ ተመራማሪው ሎውረንስ ፊሪማን አዲስ አበባ በአንዳንድ ምዕራባዊያንና የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ከተከፈተባት የስነልቡና ጦርነት ውጭ የተረጋጋችና መደበኛ እንቅስቃሴዋ ላይ ነች አሉ።

በአፍሪካ የልማት ፖሊሲ ላይ ላለፉት 30 ዓመታት ትንታኔ በመስጠትና ጥናቶችን በማድረግ የሚታወቁት ሎውረንስ ከ4 ሰዓት በፊት አዲስ አበባ መግባታቸውን በቲውተር ገፃቸው ጽፈዋል።

በመልዕክታቸውም ምሽት በሚባለው ሰዓትም ከሆቴሎች ባሻገር ቡናና ምግብ ቤቶች ክፍት እንደሆኑ፤ ቦሌ ዓለም ዐቀፍ አየር መንገድም በሙሉ አቅሙ እየሰራ እንደሆነ ለዓለም አሳውቀዋል።

ከአሜሪካ የመጡበት አውሮፕላንም ሙሉ በሚባል ደረጃ ወንበሮቹ በተሳፊሪ የተሞሉ እንደነበር መስክረዋል።

ሎውረንስ ይሄን መነሻ አድርገውም ውሸትና የተነሳሳተ መረጃ ማሰራጨታችሁን አቁሙ ሲሉ አሜሪካንና አጋሮቿን ተችተዋል።

“እዚህ (ኢትዮጵያ) አፍጋኒስታን የለም፤ የመንግሥት ለውጥም አይገባም” ሲሉ የአሜሪካንና አጋሮቿን ሴራ በግልፅ ተቃውመዋል።