ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን አስመረቀ

የካቲት 20/2013 (ዋልታ) -ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ3ሺ 700 በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ።

ዩኒቨርስቲው ያስመረቃቸው ተማሪዎች በመጀመሪያ፣ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ዲግሪ መርሃ ግብር ሲሆን ተማሪዎቹ ትምህርታቸውን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት አቋርጠው የነበሩና በተያዘው አመት ያጠናቀቁ ናቸው።

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታው ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው የፌዴራልና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።
(ምንጭ፡-ኢዜአ)