ሕዝቡ በምጣኔሃብት ግንባርም ደጀንነቱን እንዲያሳይ መንግሥት ጠየቀ

ኅዳር 20/2014 (ዋልታ) ሕዝቡ ኢትዮጵያ ባለችበት ወቅታዊ ሁኔታ 2ኛው ግንባር የምጣኔሃብቱ ጦርነትና አሻጥር ዘርፍ መሆኑን ተገንዝቦ ደጀንነቱን እንዲያሳይ መንግሥት ጠየቀ፡፡
የምጣኔሃብት ዘርፉን ለማሻሻል ከፍተኛ የሆነ እንቅስቃሴ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ተገልጿል፡፡
የበጀት ሽግሽግ በማድረግና የጎላ ፋይዳ ላላቸው ፕሮጀክቶች ቅደም ተከተል በማውጣት እየተሰራ መሆኑን የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ ዛሬ በሰጡት መግለጫቸው ተናግረዋል፡፡
የመንግሥትን ሀብት እና ንበረትም ለታለመላቸው ዓላማ እንዲውል ለማድረግ በጥብቅ ቁጥጥር እየተሰራ ነውም ብለዋል፡፡
ከልማት አጋሮች ይገኛል ተብሎ የተጠበቀው የበጀት ፍሰት ክፍትት መፍጠሩን የገለጹት ሚኒስትር ዴኤታዋ የብድር ጫናን ለማቃለል የእዳ ማሸጋሸግ ሥራ እየተሰራ መሆኑንም ገለጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ አሁን ባለችበት የኅልውና ዘመቻ ሕብረተሰቡ በጦርነቱ ግንባር ደጀንነቱን እየገለፀ መሆኑ የሚበረታታ እንደሆነ ተናግረው አሁንም ሕዝቡ ለብክነት የሚዳርጉ ወጪዎችን እንዲቀንስ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በትዝታ መንግሥቱ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!