ሕዳሴ ግድብ ለታችኛው ተፋሰስ ሀገራት መጠኑ ያልዋዠቀ የውሃ አቅርቦት እንዲደርሳቸው ያደርጋል – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ነሐሴ 19/2016 (አዲስ ዋልታ) ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የውሃ ፍሰትን በመቆጣጠርና የጎርፍ አደጋ ስጋትን በመቀነስ ለታችኛው ተፋሰስ ሀገራት በተለይ በድርቅ ዘመን መጠኑ ያልዋዠቀ የውሃ አቅርቦት እንዲደርሳቸው እንደሚያደርግ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ወደ ታችኛው የአባይ ተፋሰስ ሀገራት ተጨማሪ ብስራት ከጉባ ተደምጧል ነው ያሉት።

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የወንዝ ፍሰት ሳይስተጓጎል ከመቀጠሉም በተጨማሪ የግድቡ የውሃ ማስተንፈሻ በሮች ተከፍተው ተጨማሪ 2800 ሜትር ኪዩብ ውሃ በሰከንድ ማፍሰስ ጀምረዋል ብለዋል።

ይህ የተመዘነና የተመጣጠነ የውሃ ልቀት ግብርናን፣ የኃይል የማመንጨት ሥራን እንዲሁም በቀጣናው ያለ የሀብት አጠቃቀም ምጣኔን ለማጎልበት በእጅጉ እንደሚጠቅምም ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትናንትናው ዕለት የኅዳሴ ግድብ 3ኛው እና 4ኛው ተርባይኖች ሥራ ማስጀመራቸውን ገልጸው ሌሎቹ ዩ