መራጮች በምርጫ ሂደቱ አስፈላጊው እገዛ እና ትብብር በምርጫ አስፈጻሚዎች እየተደረገላቸው መሆኑን ገለጹ

ሰኔ 14/2013 (ዋልታ) – በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ ምርጫ ክልል 2/14 ምርጫ ጣቢያ 04 ታዛቢዎች በተገኙበት ቃለ ጉባኤ ተይዞ የድምጽ መስጫ ሳጥኖች ተከፍተው ህዝቦች እየመረጡ ይገኛሉ።

በምርጫ ጣቢያው የክፍለ ከተማው የብልጽግና ፓርቲ እጩ የሆኑት ዶክተር ብርክታዊት አደራ  ተገኝተው መርጠዋል።

በምርጫ ጣቢያው 780 መራጮች ካርድ ወስደዋል፡፡

በምርጫ ጣቢያው አቶ ክፍለ ማሪያም ከአዲስ ትውልድ ፓርቲ፣ አቶ ደረጀ ከኢዜማ ተገኝተው ድምጽ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

(በብርሃኑ አበራ)