መጋቢት 15/2014 (ዋልታ) መስፍን ጣሰው አዲሱ የአየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆነው መሾማቸውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ።
አዲሱ ተሿሚው በኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ38 ዓመታት በላይ ያገለገሉ መሆናቸውም ተጠቁሟል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ተወልደ ገብረማርያም ባጋጠማቸው የጤና እክል ምክንያት ከኃላፊነታቸው በፈቃዳቸው መልቀቃቸውን በትላንትናው እለት አየር መንገዱ ማስታወቁ ይታወሳል።
በትዕግሥት ዘላለም
ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
ቲዊተር https://twitter.com/walta_info
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!