መንግሥት ለምጣኔ ሃብት እድገት በትኩረት እየሠራ መሆኑን ም/ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን ገለጹ

መንግስት ለምጣኔ ሀብቱ እድገት እና ስኬታማነት በትኩረት እየሠራ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገልጸዋል።

1 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ፈሰስ የተደረገበት የዳሽን ቢራ የማስፋፊያ ፕሮጀክት በደብረ ብርሃንና ጎንደር ተመርቋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ የማስፋፊያ ፕሮጀክቶች በአገር ኢኮኖሚ ውስጥ ከፍተኛ ሚና ያላቸው በመሆኑ ሁሉም በትብብር እና በትኩረት መስራት ይጠበቅበታል ብለዋል።

እንደ አገር የገጠመንን የሰላምና የልማት ችግሮች በመፍታት ለቀጣይ ትውልድ የተሻለች አገርን ለማስረከብ አንድነታችንን ማጠናከር ይገባል ሲሉም ተናግረዋል፡፡

በመርኃ-ግብሩ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንን ጨምሮ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል እና ሌሎች የፌደራልና የክልል የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

 

በብርሃኑ አበራ