መንግሥት ዓለም አቀፍ ገለልተኛ ተቋማት እውነቱን እንዲያጣሩ እየሰራሁ ነው አለ

ታኅሣሥ 2/2014 (ዋልታ) – የተለያዩ ዓለም ዐቀፍ ገለልተኛ ተቋማት ወደ ኢትዮጵያ በመመምጣት እውነታውን እንዲያጣሩና እውነትን እንዲያወጡ የማድረግ ሥራ በመንሥት በኩል እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ፡፡

የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታዋ ሰላማዊት ካሳ በሰጡት መግለጫ የሽብር ቡድኑ ተወረው በነበሩ የአማራና አፋር ክልል ጅምላ ጭፍጨፋን ጨምሮ የሰብኣዊ መብቶች መታሱን ተከትሎ ዓለም ዐቀፉ ማኅበረሰብ እውነታውን እንዲረዳ መንግሥት እየሰራ ነው ብለዋል፡፡

እነዚህን የሽብር ቡዶኖች (ኃይላት) ተጠያቂ ለማድረግም ይሰራል ነው ያሉት፡፡

የሽብር ቡድኑ ተወረው በነበሩ የአማራና አፋር ክልል ጅምላ ጭፍጨፋ ማድረጉን ሂውማን ረይትስዎች ማስታወቁን አስታውሰዋል፡፡

አሸባሪው በወረራቸው አካባቢዎች ያደረሳቸውን ጥፋቶች በመለዬት ክስ የመመስረት ሥራን የሚከውን ግብረ ኃይል ተቋቁሞ እየተሰራ መሆኑንም አሳውቀዋል፡፡

ግብረ ኃይሉ በተመሳሳይ የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም ይሰራል፤ ኢትዮጵያ በምትመራባቸው ዓለም ዐቀፍ ሕግጋትንም በመከተል ተጠያቂ ለማድረግ ይሰራል ብለዋል፡፡