መንግሥት የተመረጡ የጁንታውን ወታደራዊ ዐቅሞች ስለሚመታ በትግራይ የሚኖሩ ወገኖች አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መከረ

ነሐሴ 20/2014 (ዋልታ) መንግሥት እስከ አሁን ድረስ ለሰላም በሩን ክፍት አድርጎ ቢጠባበቅም ጁንታው ጥቃቱን ቀጥሎበታል ሲል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ገልጿል።
በመሆኑም የፌዴራል መንግሥት ያለ ቅድመ ሁኔታ ለመነጋገር የገለጸው ዝግጁነት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ለጁንታው ፀረ ሰላም ዕብሪት ምንጭ የሆኑ ወታደራዊ ዐቅሞችን ዒላማ ያደረገ እርምጃ ይወስዳልም ብሏል።
ስለሆነም በትግራይ የምትኖሩ ወገኖቻችን በተለይም የጁንታው ወታደራዊ መሣሪያዎች እና ማሠልጠኛዎች ካሉባቸው አካባቢዎች ራሳችሁን እንድታርቁ ይመከራል ሲል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አሳስቧል።