መንግሥት የአሸባሪው ቡድንን ጥፋት ለማውገዝ ያልደፈሩ አካላትን ወቀሰ

ታኅሣሥ 5/2014 (ዋልታ) አሸባሪው የሕወሓት ቡድን በኢትዮጵያ አያሌ ግፎችን ሲፈፅም ለማውገዝም ሆነ ለመተቸት ያልደፈሩ አካላትን መንግሥት ወቀሰ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የሽብር ቡድኑ የተቀደሰውን እና በዓለም ቅርስነት የተመዘገበውን ቅዱስ ላሊበላ ሲያረክስ የተባበሩት መንግሥታት ተቋም የሆነው ዩኒስኮ ዝምታን መምረጡን አንስተዋል።
የዓለም ጤና ድርጅት በበኩሉ ይኸው የሽብር ቡድን በሺሕዎች የሚቆጠሩ (አማራ ክልል ላይ ብቻ ከ2 ሺሕ በላይ የጤና ተቋማትን አውድሟል) የጤና ተቋማትን ሲዘርፍና ሲያወድም ድርጊቱን ለመኮነን አለመፈለጉን አምባሳደር ሬድዋን አስምረውበታል፡፡
የአውሮፓ ኅብረትም ቢሆን በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ተጠምዶ ሲያሴር እንደሚውል ያስታወሱት ሚኒስትር ዴኤታው ለኢትዮጵያ ወዳጆች ትክክለኛ አጋነትን የሚያሳዩበት ወሳኙ ጊዜ አሁን ነው ሲሉ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ገልጸዋል፡፡