መከላከያ ሚኒስቴር የብረት የጥሬ እቃዎችን ሊያቀርብ ነው

ሚያዝያ 26/2014 (ዋልታ) የብረት አምራቾች ያለባቸውን የጥሬ እቃ ችግር ለማቃለል ከመከላከያ ሚኒስትር እና በስሩ ካሉ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች የብረት ግብአቶችን እንዲያገኙ ስምምነት ላይ መደረሱን የማዕድን ሚኒስትር ታከለ ኡማ አስታወቁ።
ለአመታት ተከማችተው የቆዩና የወዳደቁ ብረቶችን ወደ ምርት መቀየር በአፋጣኝ ችግሩን ለማቃለል እንደሚረዳ እና ብረቶቹ ወደ አምራቾቹ በፍጥነት ማቅረብ እንደሚጀመር ተጠቁሟል።
ዘላቂነት በሀገር ውስጥ የብረት ማዕድንን ለማውጣትና አምራቾች ጥሬ ግብአቱን ከሀገር ውስጥ ማግኘት እንዲችሉ እንቅስቃሴ መጀመሩንም ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት አስታውቀዋል፡፡