መከላከያ ሠራዊት በወሰደው ርምጃ የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች እጅ እየሰጡና እየተበተኑ መሆኑ ተገለጸ

ጥቅምት 15/2015 (ዋልታ) የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በወሰደው ከባድና ፈጣን ርምጃ የሕወሐት ታጣቂዎች አብዛኞቹ የተበተኑና እጅ የሰጡ ሲሆን ሌሎች ደግሞ በተሳሳተ መረጃ ተደናግረው ምን ማድረግ እንዳለባቸው ግራ እንደተጋቡ መረጃዎች አመልክተዋል።

በቅርቡ ለመከላከያ እጅ የሰጡ የአሸባሪው ሕወሓት ታጣቂዎች የክፋት አዝማቾቻቸውን ሁኔታ በአንድ ጥሩ የትግርኛ ምሳሌያዊ አነጋገር ገልጸውታል።
ምሳሌያዊ አነጋገሩ “ማሽላውን ከአደጋ ለመከላከል የከበበው አጥር ለማሽላው እንጂ ራሱ አጥሩን አልጠቀመውም” የሚል ሲሆን ይሄም ጁንታው እንጂ ታጣቂዎቹ ከጦርነቱ ያተረፉት እልቂት ብቻ መሆኑን ያሳያል።
በመሆኑም የተበተኑና ከጁንታው የጥፋት ወጥመድ ማምለጥ የሚፈልጉ የጁንታው ታጣቂዎች መከላከያ ወደ ተቆጣጠራቸው የትግራይ አካባቢዎችና ወደ አጎራባች ክልሎች በመሄድ እጃቸውን በሰላም እንዲሰጡ የመከላከያ ሠራዊት ጥሪ ያቀርባል።
እጃቸውን ለሚሰጡ የጁንታው ታጣቂዎች አስፈላጊው ክብካቤ እንዲደረግ መመሪያ ተላልፏል።

የአጎራባች ክልሎችና ከህወሓት የተላቀቁ የትግራይ አካባቢዎች ሕዝብ፣ እጅ የሚሰጡ የጁንታው ታጣቂዎችን በመቀበል፣ ተንከባክቦ ለመከላከያ ሠራዊቱ እንዲያስረክብ መከላከያ መልእክት ማስተላለፉን የመከላከያ ሰራዊት መረጃ አመላክቷል፡፡።