ሐምሌ 19/2013 (ዋልታ) – የሀገር መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍና የህወሓት ቡድንን የሚቃወም ህዝባዊ ሰልፍ በጋምቤላ ከተማ እየተካሄደ ነው።
ሰልፈኞቹ “የአብሮነት ጉዟችን በሽብርተኞች አይደናቀፍም”፣ “እኛ ጋምቤላዎች ከመከላከያ ሠራዊታችን ጎን ነን”፣ “ሰላማችን በአንድነታችን ይጠበቃል”፣ “ክብርና ሞገስ ውድ ህይወታቸውን ለሰጡ የመከላከያ ሠራዊት አባላት”፣ “ኢትዮጵያ በጀግኖቿ አፍራ አታውቅም”፣ “አገር በጁንታው ሴራ አትፈርስም”፣ “የህልውናችን መሠረት የሆነው የህዳሴ ግድባችንን እስከመጨረሻው በመደገፍ ከዳር እናደርሳለን”፣ “ጁንታው የኢትዮጵያ ነቀርሳ ነው” የሚሉ መፈክሮችን በመያዝ ወጥተዋል።
ሠራዊቱን በሚደግፈውና ሽብርተኛውን የህወሓት ጁንታ በሚያወግዘው ሰልፍ ላይ በርካታ የጋምቤላ ከተማ ነዋሪዎች፣ የመንግስት ሰራተኞችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች መሳተፋቸውን ከክልሉ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽህፈት ቤት ያገነነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ህወሓት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪ ቡድን ተብሎ መፈረጁ የሚታወቅ ነው፡፡