መከላከያን ለሚቀላቀሉ የደሴ ወጣቶች ሽኝት

መከላከያን ለሚቀላቀሉ የደሴ ወጣቶች ሽኝት

መስከረም 10/2014 (ዋልታ) የአገር መከላከያ ሰራዊትን ለመቀላቀል የተመዘገቡ የደሴ ከተማ ወጣቶች ሽኝት ተደረገላቸው።

ቅዳሜ በ10 ሺሕዎች የሚቆጠሩ የአካባቢው ወጣቶች የፌደራል መንግሥት ያቀረበውን ጥሪ ተቀብለው መከላከያን ለመቀላቀል መዘጋጀታቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

በዕለቱ የአገር ሉኣላዊነት መከታ የሆነውን የመከላከያ ሰራዊት ማጠናከር ስለሚቻልበት ስልትም ከወጣቶቹ ጋር ምክክር ሲደረግ መዋሉ ይታወቃል።

በተለያዩ ክልሎች መከላከያን የሚቀላቀሉ ወጣቶች ወደ ስልጠና ማዕከላት ሽኝት እየተደረገላቸው እና ስልጠናቸውንም አጠናቀው እየተመረቁ ይገኛሉ። በዚህም ኢትዮጵያዊያን የአገር መከላከያ ሰራዊትን እያጠናከሩ ነው።

ይህ ለአገርና ሕዝብ ዘብ የመቆም ዘመቻ የመንግሥት ምስጋና የተቸረው ሲሆን ተጠናክሮ እንዲቀጥልም እየተጠየቀ ነው።